Homepage video
በኢትዮጲያ በ2022/30 በ10 ሺህ ተሸከርካሪ የሚደርሰውን የመንገድ ትራፊክ የሞት አደጋ 10 ማድረስ
በኢትዮጲያ በ2014 የደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ሞት ቁጥር 3,971(በ10 ሺህ ተሸከርካሪዎች 29 ሰዎች)፣ ከባድ አካል ጉዳት በሰው 5,586፣ቀላል ጉዳት በሰው 4,793 እና ንብረት ውድመት በብር 13,509,248,087 ነው፡፡

ስለ እኛ

በኢትዮጲያ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለማረጋገጥ ለረዥም አመታት የተለያዩ ተቋማትሀላፊነት ተሰጥቷቸው ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎችቀርፀው እና ተግባራዊ በማድረግ ሀላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡ የቅድመየመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ከማረጋገጥ እና የድህረ አደጋ ጉዳትን ከማሳነስ አንፃርበአዋጅ ቁጥር 468/98 ለቀድሞ ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የህብረተሰብንግንዛቤ የመፍጠር፣ የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት ከማረጋገጥ ጋርተያይዞ ሀላፊነት ተሰጥቶ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 559/2000ና 799/2005 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 300/2006 እና 205/2003 ለመድን ፈንድ ፅ/ቤት እና ለመደንፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ለተጎጂዎች የካሳ ክፍያ የመክፈል፣ የአስቸኳይ ህክምናእንዲያገኙ የማድረግ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶች እንዳይጋለጡየማድረግ እንዲሁም የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተማማኝና ከአደጋ የፀዳእንዲሆን የማድረግ ሀላፊነቶችን ተሰጥቶት የተለያዩ ስራዎች ይከናወኑ ነበር፡፡

READ MORE

አሁኑኑ ይመዝገቡ

ወርሐዊ መርጃዎችን ያግኙ