ስለ እኛ

በኢትዮጲያ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለማረጋገጥ ለረዥም አመታት የተለያዩ ተቋማትሀላፊነት ተሰጥቷቸው ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎችቀርፀው እና ተግባራዊ በማድረግ ሀላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡ የቅድመየመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ከማረጋገጥ እና የድህረ አደጋ ጉዳትን ከማሳነስ አንፃርበአዋጅ ቁጥር 468/98 ለቀድሞ ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የህብረተሰብንግንዛቤ የመፍጠር፣ የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት ከማረጋገጥ ጋርተያይዞ ሀላፊነት ተሰጥቶ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 559/2000ና 799/2005 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 300/2006 እና 205/2003 ለመድን ፈንድ ፅ/ቤት እና ለመደንፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ለተጎጂዎች የካሳ ክፍያ የመክፈል፣ የአስቸኳይ ህክምናእንዲያገኙ የማድረግ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶች እንዳይጋለጡየማድረግ እንዲሁም የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተማማኝና ከአደጋ የፀዳእንዲሆን የማድረግ ሀላፊነቶችን ተሰጥቶት የተለያዩ ስራዎች ይከናወኑ ነበር፡፡

ሆኖም ስራዎችን አቀናጅቶ በአንድ ላይ ለመምራት ይቻል ዘንድ በአዲስ መልክየመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በአዋጅ ቁጥር 1263/2013 በሚንስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 493/2014 ተቋቁሞ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትግንዛቤን በማሳደግ የመንገድ ትራፊክ ለተጠቃሚዎች ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ለአጋየማያጋልጥና ፍሰቱ የተሳለጠ እንድሆን በማድረግ በህብረተሰቡ ላይ በመንገድ ትራፍክ አደጋማክንያት የሚደርሰውን የሞት፣ የአካል እና የንብረት ጉዳት መቀነስ፤ በተሽከርካሪ አደጋምክንያት የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ጉዳት ለሚደርስባቸው ተጎጂዎች ካሣ በመክፈል፣ የስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንድያገኙ በማድረግ እና ተጨማሪ ጉዳቶች እንዳይደርሱበማድረግ በአደጋ ተጎጅዎች ላይ የሚደርስባቸውን ኢኮኖሚያዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችመቀነስ እና የመንገድ ትራፍክ ደህንነት አስተማማኝ እና ከአደጋ የጸዳ እንዲሆን የማድረግሀላፊነት ተሰጥቶት ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ተልዕኮ

የቅድመ እና የደህረ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና ህጎች በመቅረጽና ሥራ ላይ በማዋል፣ የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማሳደግ፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማረጋገጥ እንዲሁም  ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የተቀናጀና የተቀላጠፈ  አሰራሮችን በመፍጠር  የትራፊክ አደጋን በመቀነስ እና የሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ የዜጎች ደህንነትና ምቾትን ማረጋገጥ ነው፡፡ 

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የመንገድ ትራፊክ አደጋ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር  የማይሆንባት ኢትዮጵያን ማየት፡፡ 

ግብ

በትራፊክ አደጋ የሚደርስን የሞት አደጋን በ2030 በ50% መቀነስ

እሴቶች

 ተደራሽነት፣

  •  ፍትሀዊነት፣
  •  አገልጋይነት፣
  •  ተጠያቂነት፣
  •  አጋርነት፣

 

የሥራ አመራር ቦርድ

ባለድርሻ አካላት