የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ጋር በጋራ ሲያበለፅጉት የቆዩትን የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (Road Accident Data Management System – RDMS) በይፋ ተረክቧል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው፣ የመረጃ ሥርዓቱን በተረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ሲስተሙ በመላው ሀገራችን ለሚገኙ የፖሊስ ሠራዊት አባላትና የትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል። ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል አክለውም የመረጃ ሥርዓቱ ከመተግበሩ በፊት ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን እንዲሁም የሙከራና የማስተዋወቅ ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል። አሁን ላይ ሲስተሙ ወደ ሙሉ አቅም ትግበራ መግባቱን የገለፁት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል የክልል ፖሊስ አመራሮችና የትራፊክ ዘርፍ ባለሙያዎች ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በዳታቤዙ ውስጥ በማስገባት የተሟላ የመረጃ ሥርዓት እንዲገነባ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች፣ ባለንብረቶች፣ ኢንሹራንስ ሰጪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ የሚያገኙበት የመረጃ ሥርዓት መሆኑን የገለጹት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት በተደራጀና በተተነተነ መረጃ የትራፊክ አደጋ መንሥኤዎች ላይ ተመስርተው መረጃ መር ውሳኔዎችን በመስጠት የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። “ከአሁን በኋላ ትክክለኛ የትራፊክ መረጃዎችን ሌላ ሰው ሊነግረን አይገባም” ያሉት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመረጃ ሥርዓቱ ተግባራዊነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ እና በዚህ ሥራ ላይ በማንኛውም ሁኔታ ወደ ኋላ የሚቀር ክልል ወይም አካባቢ ሊኖር አይገባም ሲሉ መመሪያ ሰጥተዋል። ክቡር አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው አዲሱ የዲጂታል አሰራር ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከወረዳ እስከ ፌደራል በወረቀት ይላኩ የነበሩ፣ ታማኝነት የጎደላቸውና ወጥ ያልሆኑ የሪፖርት መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በሀገራችን የመንገድ ደህንነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዳታ ላይ ተመስርቶ በጋራ ለመገምገምና ለመፍታት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አነስተኛ የተሽከርካሪ ቁጥር ያላት ቢሆንም ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ከሚመዘገብባቸው ሀገራት ተርታ መሰለፏንና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ጋር ወጥ በሆነ መረጃ ላይ አለመስማማት መኖሩን አንስተው ችግሩን ለመቅረፍ ሲስተሙን ዲጂታላይዝ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
በትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት አፈፃፀም ላይ ጥናታዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ፤
ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም አዳማ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት አፈፃፀም ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ ። የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ በመክፈቻ ንግግራቸው የትራፊክ አደጋ በዓለም ብሎም በሀገራችን አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ የዜጎችን ህይወት በመቅጠፍ እና ከፍተኛ የሆነ የሀገርን ኢኮኖሚ እያንገዳገደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ይህንን ችግር ለመፍታት የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት በማልማት ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል፡ ይህንን ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ወጥና ተዓማኒ የሆነ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት መዘርጋታ እንደሚገባ ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል በበኩላቸው እንደገለፁት በዓለም ቀዳሚ የሆነውን የትራፊክ አደጋ መረጃ አሰባሰብ ስርዓት በሀገር አቀፉ ደረጃ ወጥ በማድረግ ተዓማኒ መረጃ መሰብሰብ እና መተንተን የሚያስችል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት አሰራርና አፈፃፀም ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ አበራ እሸቱ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የአይ ሲቲ ስራ አሰፈፃሚ እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮ/ር ጥላሁን ወ/ ትንሳዔ የትራፊክ እና ወንጀል ኢንተለጀንስ ጥናትና ትንተና መምሪያ ኃላፊ አቅርበዋል። በመጨረሻም የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓቱ ወደ ተግባር ያልገቡ ክፍለ ከተሞችና ክልሎች በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል :: በውይይት መድረኩ የተሳተፉ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ11ድ ክፍለ ከተሞች፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ሸገር ሲቲ ፖሊስ ኮሚሽን ከ12ቱ ክፍለ ከተማ ኮሚሽነሮችና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የህዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው!
ከአምናው 9ወር ጋር ሲነፃፀር የትራፊክ አደጋው መቀነሱ ተገለፀ
ከአምናው 9ወር ጋር ሲነፃፀር የትራፊክ አደጋው መቀነሱ ተገለፀሲዳማ ክልል ሀዋሳ 2018 ዓ.ም የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ባለሙያዎች ድጋፍ፣ ክትትል እና መልከታ ለማድረግ በተገኙበት በመጀመሪያው ዕለት የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ኮረኔል ሮዳሞ ኪአ በመክፈቻ ንግግራቸው ከአምናው 9ወር ጋር ሲነፃፀር የትራፊክ አደጋው መቀነሱ ገልፀዋል።ይህን ተከትሎም ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተወጣጡ ባለሙያዎች በተገኙበት ለመንገድ ደህንነት መረጋገጥ እና አስቸኳይ ህክምና መተግበር ይበልጥ አስተዋጽኦ ያላቸው የጤና ተቋም ፣የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ፣ የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት እና በትምህርት ቤት የመንገድ ደህንነት ክባት ያሉበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አከናውነዋል።በቀጣይ ቀናትም የአሽከርካሪዎች ስልጠና እና ሌሎች ተግባሮችም የሚከናወኑ ይሆናል።
CRISIS ON THE CORRIDORS: ETHIOPIA’S BATTLE TO RECLAIM THE “DEADLY ROADS”
ADDIS ABABA — In a high-stakes move to curb the rising tide of traffic fatalities, the Ethiopian Road Safety and Insurance Fund has unveiled a sweeping modernization project aimed at transforming the country’s most hazardous transit routes. Teaming up with the World Bank, road safety officials are shifting from traditional enforcement to a data-driven, life-saving strategy. At the heart of this new initiative is a focus on the “Golden Hour”—the critical 60-minute window after a crash where medical intervention determines whether a victim survives or becomes another statistic. The Target: Ethiopia’s “Black Spots” After a rigorous 2,000-kilometer engineering study, officials have identified four primary “Deadly Roads” where death rates per kilometer have reached alarming peaks: Addis Ababa – Adama Expressway Addis Ababa – Debre Berhan Batu – Shashamane Butajira – Hossana These corridors are now the frontline for a new arsenal of safety tech, including advanced speed radars and high-tech rescue vehicles equipped with hydraulic cutters to extract victims trapped in wreckage. The “Five Killers” Under Fire The project coordinator identified five specific behaviors that are fueling the carnage: Speeding: Described as the nation’s #1 killer. Distracted Driving: Motorists increasingly texting or watching videos behind the wheel. Seatbelt Neglect: Particularly in public transport (minibuses), where passengers are most vulnerable. Impaired Driving: Driving under the influence of alcohol, Khat, or even cigarettes. Motorcycle Safety: Lack of standardized helmets and overcrowding. Safety Standard Update: New legal standards adopted in late 2024 mandate high-quality, strapped helmets to protect against severe head trauma, moving away from “construction-style” helmets that offer zero protection. A Culture of Caution The report didn’t just blame the roads; it called out a culture of risk. Footage shared during the briefing showed the terrifying reality of “hanging”—passengers clinging to the back of moving minibuses and “Dolphin” vans to save on fare, a practice that frequently leads to fatal falls. “No one should die because they need to get somewhere,” the agency stressed. As Ethiopia rolls out the “Platinum Ten”—a protocol to provide basic life-saving aid within the first ten minutes of a crash—the message to the public is clear: technology and law can build a safer road, but the driver’s hand on the wheel remains the final line of defense.
በብሄራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ የግማሽ ዘመን አፈፃጸም ላይ ወይይት እየተደረገ ነው
ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ቢሾፋቱየመንገድ ደህንነት ዘርፍ ከ2021-2030 እ.ኤ.አ የተቀመጡ አለማቀፍ ግቦችን ለማሳካት ከሃገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመ ብሄራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ የግማሽ ዘመን አፈፃጸም ግምገማ (Midterm Evaluation) የፌደራል፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት አመራሮችና ባለሞያዎች በተገኙበት በአፈፃፀም ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።