በድሬደዋ አስተዳደር ግንቦት 30 እስከ ሰኔ 24 ሲካሄድ በነበረው ሀገር አቀፍ የቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መረሃ ግብር ውጤታማ እንደነበር ተጠቆመ

16 Feb 2019

በድሬደዋ አስተዳደር ግንቦት 30 እስከ ሰኔ 24 ሲካሄድ በነበረው ሀገር አቀፍ የቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መረሃ ግብር ውጤታማ እንደነበር ተጠቁሟል።

በመርሀግብሩ በአስተዳደሩ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን እና ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ላይ ያስተዋልነው ቅንጅታዊ አሰራር በሌሎች ክልሎችም እንደተሞክሮ ሊወሰድ ሚገባ ነው አሉ በመርሀግበሩ የተሰማሩ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ባለሙያዎች።

,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,

በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት ከግንቦት 30 ጀምሮ የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን፣ የቦሎ የዕድሳት ጊዜ ያለፍባቸውና የቴክኒክም ምርመራ ያላደርጉ፣ ቀበቶ ፣ የመረጃ ፍቃድ የዕድሳት ጊዜው ያለፈበት እና ፍቃድ ሳይኖራቸው የመስታወት ማጥቆሪያ ስቲከር እየተጠቀሙ የተያዙ አሸከርካሪዎች ላይ የቁጥጥር እንደሁም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ በገበያ ቦታዎች እና እምነት ተቋማት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን ሰኔ 25 ማጠቃለያውን አድርጓል።

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለኝታ አባይነህ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ እንደተናገሩት በዘመቻው በከተማችን ለትራፊክ አደጋ መነሻ ናቸው ተብለው በተለዩ ችግሮች ላይ ሰፊ ቁጥጥር በማካሄድ እንዲሁም ማህበረሰቡን በተለያዩ መንገዶች በመንገድ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ላይ ግንዛቤን በማስጨበጥ ሰፊ ለውጦች መገኘታቸውን ጠቁመው ለዚህም በዘመቻው የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል። መሰል የቁጥጥር ስራዎችን እንደባለስልጣን መስሪያቤት ከትራፊክ ባለሙያዎቻችን ጋር በመቀናጀት በስፋት እያከናወንን እንገኛለን ያሉት ወ/ሮ አለኝታከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ባለሙያዎች ከኛ ጋር መቀናጀት በተሻለ አቅም እና ቅንጅት እንድንሰራ አስችሎናል ብለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅ/መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ይሄነው ሽፈራው በበኩላቸው በቅንጅት መስራታችን ከአመት አመት በመንገድ ላይ ሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን በአብላጫው ማስወገድ መቻሉን የጠቆሙ ሲሆን ይኸም በቀጣይም ተጠናክሮ ለትራፊክ አደጋ መከሰት መንስኤ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት በስፋት ይሰራል ብለዋል። አንድም ዜጋችንን በትራፊክ አደጋ እንዳናጣ ተግተን እንሰራለን ብለዋል።

ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በመርሀግብሩ የተሳተፉ ባለሙያዎች በበኩላቸው ቀላል ጥፋት የፈፀሙ አሸከረካሪዎች እና የግንዛቤ ክፍተት ላለባቸው የማስተማር ስራ መሰራቱን ጠቁመው በዘመቻው ግን በአስተዳደሩ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን እና ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ላይ ያስተዋሉት ቅንጅታዊ አሰራር በሌሎች ክልሎችም እንደተሞክሮ ሊወሰድ ሚገባ ነው ብለዋል።

መረጃው የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ነው